Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ በሀዋሳ ከተማ ያስገነባው የአቪዬሽን ማሰልጠኛ ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀዋሳ ከተማ ያስገነባው የአቪዬሽን ማሰልጠኛ ማዕከል ተመርቆ ተከፈተ፡፡

ማዕከሉን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ መርቀው ከፍተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉትም÷የሀዋሳ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአጭር ግዜ  ውስጥ ተደራጅቶ ይህን ማሰልጠኛ ተቋም ማቋቋሙ የሚበረታታ ነው።

ወደ ክልሉ የሚመጡ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎችና እንግዶች የዚህ አየር መንገድ ተጠቃሚ መሆናቸው በመግለፅ የተለያዩ ማስፋፊያዎች እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

የክልሉ መንግስትም ተቋሙ ለሚፈልገው ትብብር ከጎኑ እንደሆነ ማረጋገጣቸውን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቆ፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስን ጣሰው፣ የሲዳማ ክልል የስራ ሃላፊዎችና የኢትዮጵያ አቬሽን አካዳሚ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.