Fana: At a Speed of Life!

ቭላድሚር ፑቲን እና ሺ ጂንፒንግ የተለያዩ ሥምምነቶችን ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቻይናው አቻቸው ሺ ጂንፒንግ የተለያዩ ሥምምነቶችን ተፈራረሙ።
 
ሥምምነቶቹ ሀገራቱ በንግድ፣ በኢንዱስትሪ፣ በሳይንስ እና ወታደራዊ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክሩ ናቸው ተብሏል።
 
መሪዎቹ ከሥምምነቱ ባለፈ የሀገራቱን የንግድ ግንኙነት ማሳደግና ድንበር ተሻጋሪ መሰረተ ልማት ማስፋፋት በሚቻልበት አግባብ ላይ መምከራቸውን አር ቲ ዘግቧል።
 
ከዚህ ባለፈም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በግብርናው ዘርፍ ትብብር ለማድረግና በኃይል ዘርፍ የሚያደርጉትን ትብብር ማሳደግ በሚያስችል አግባብ ላይም መክረዋል።
 
በመከላከያ ዘርፍም ሀገራቱ በየጊዜው የባህር እና አየር ኃይል ልምምድ እና ቅኝት ለማድረግ ብሎም በጦር ኃይላቸው መካከል ያለውን ትብብር በማሳደግ ያለውን መተማመን ለማሳደግም ተሥማምተዋል።
 
መሪዎቹ የሩሲያ ዩክሬን ግጭትም በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት መግባባት ላይ ደርሰዋል ነው የተባለው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.