Fana: At a Speed of Life!

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ በተመድ የውሃ ጉባዔ እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ በኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የውሃ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

ጉባዔው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ በታጂክስታን እና ኔዘርላንድስ መንግስት ነው የተዘጋጀው፡፡

ድርቅና የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተለውን ተጽዕኖ፣ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ፋይዳ፣ የግብርና ሥራዎችን እና የውሃ ሀብት ትብብርን በተመለከተ ሚኒስትሩ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ዮሴፍ ካሳዬን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች በመድረኩ እየተሳተፉ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.