Fana: At a Speed of Life!

የዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ ዘንድሮ ከመከላከያ ጡረታ መውጣቴ ቁርጥ ነው አሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ ጀነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ዘንድሮ ከሀገሪቷ መከላከያ በጡረታ እንደሚወጡ በትዊተር ገፃቸው አስታወቁ፡፡

የጦር ጄኔራሉ በትዊተር ገጻቸው ይህን ያሉት በዩጋንዳ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ለ30 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ካገለገሉ በኋላ መሆኑን ቢቢሲ አስታውሶ ዘግቧል፡፡

ያሁኑ ጀኔራል ካይኔሩጋባ አምና መጋቢት ወር ላይ የምድር ጦር አዛዥ በነበሩበት ወቅትም ተመሳሳይ የ“ጡረታ መውጣቴ ነው” መልዕክት በትዊተር ገጻቸው አስነብበው ነበር ተብሏል፡፡

ነገር ግን በወቅቱ መከላከያ ኃይሉ የፕሬዚዳንቱን ልጅ የጡረታ ጥያቄ ውድቅ እንዳደረገባቸው እና ሥራቸውን እንደቀጠሉ ተነግሯል፡፡

ጄኔራሉ በፈረንጆቹ 2026 ላይ ለፕሬዚዳንትነት እወዳደራለሁ ብለው በትዊተር ገጻቸው ካሰፈሩ በኋላ ያስነበቡትን ሐሳባቸውን መልሰው መሰረዛቸውንም ዘገባው አስነብቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.