Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የምግብ ዋስትናን በዘመናዊ ግብርና ለማረጋገጥ በትኩረት ይሠራል – አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል በዘመናዊ የግብርና ልማት እስትራቴጂ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገለጹ፡፡

በክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ቢሮ በዘላቂ የልማት ግብ በጀት ድጋፍ በላሬና፣ በአቦቦ ወረዳዎች የሚገነቡ መስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶች የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል።

አቶ ኡሞድ ÷የመስኖ ግንባታዎቹ በተያዘላቸው የስድስት ወራት ጊዜ ገደብ ውስጥ መጠናቀቅ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ማኅበረሰቡ በግለሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጡ ማስቻል ይገባል ብለዋል።

በመስኖ ልማት በዓመት ሁለት ጊዜ እና ከዛ በላይ ጊዜ እንዲያመርት እንሠራለንም ብለዋል፡፡

የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኮንግ ጆክ ÷ በላሬ ወረዳ ኖር ቀበሌና በአቦቦ ወረዳ ቾቦ ኪር ቀበሌ መሰረተ ድንጋይ የተቀመጠላቸው ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ 121 ሄክታር መሬት እንደሚያለሙና 280 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቶቹ 149 ሚሊየን 81 ሺህ 874 ብር በሆነ ወጪ እንደሚገነቡ ገልጸው÷ በላሬ ወረዳ ኖር ቀበሌ የሚገነባው 98 ሚሊየን 754 ሺህ 437 ብር ሲሆን÷ በአቦቦ ወረዳ ቾቦ ኪር ቀበሌ ደግሞ 50 ሚሊየን 327 ሺህ 437 ብር እንደሆነ አመልክተዋል።

በግንባታ ሂደት እና በእድሳት ላይ ያሉት ሥምንት የመስኖ ፕሮጀክቶችም ወደ ሥራ እንዲገቡ ለማድረግ ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.