Fana: At a Speed of Life!

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከቻይናው የጨርቃ ጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪ ጋር ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከቻይናው የጨርቃ ጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪ ጋር ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች ለዓለም አቀፍ ገበያ ብቁ ለማድረግ የሚያስችል ስልጠና ለመስጠት ነው ተብሏል።

የኦሪየንት ኢንተርናሽናል ሆልዲንግ ሊቀመንበር ቶንግ ጂሸንግ እንዲሁም በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክ እና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ተገኝተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው እንደገለፁት የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በማሳደግ ትልቅ አቅም ያለው ዘርፍ ነው።

ከዚህ አንጻርም ይህን ከግብ ለማድረስና ኢንዱስትሪውን የሚመጥን የሰለጠነ የሰው ሀይል በማብቃት ረገድ ተቋሙ ሚናውን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።

በየዛሬው ስምምነትም ይህንን የሚያጠናክር እና የሚደግፍ መሆኑን አስረድተዋል።

ይህ ስምምነት 4 ሺህ 500 ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የስራ ዕድል እንደሚፈጥርም ነው የተገለፀው።

የኦሪየንት ኢንተርናሽናል ሆልዲንግ ሊቀመንበር ቶንግ ጂሸንግ በበኩላቸው፥ የስራ ዕድል እና ስልጠናዎችን ለማጠናከር እንዲሁም አዳዲስ የሞያ ማበልፀግ ስራዎችን በተግባር ለማዋል በዛሬው እለት 100 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ወደ ቻይና በመላክ ለማስልጠን መታቀዱን ጠቁመዋል።

 

 

በታሪኩ ወልደሰንበት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.