Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ያለውን የገበያ ሁኔታ ለማረጋጋት በቅንጅት እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ እና የአዲስ አባባ ንግድ ቢሮዎች መጪዎቹን በዓላት መሰረት በማድረግ በመዲናዋ ያለውን የገበያ ሁኔታ ለማረጋጋት በጋራ እየሠሩ መሆኑን ገለጹ፡፡

በዚሁ መሰረት በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ዩኒየን አማካኝነት ከ62 ሺህ ኩንታል በላይ እህል በአዲስ አበባ ለሚገኙ የሸማቾች ኅብረት ሥራ ዩኒየኖች ተከፋፍሏል፡፡

በዛሬው ዕለትም አቅርቦቱ ወደ ኅብረት ሥራ ማኅበራት መጋዘኖች ተከፋፍሏል፡፡

የኦሮሚያ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ዳንኤል ቸርነት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ ከ2 ሺህ 700 ኩንታል በላይ ጤፍ ዛሬ በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ዩኒየኖች በኩል ለከተማው ሕብረተሰብ ቀርቧል፡፡

በንፋስ ስልክ እና በኮልፌ ክፍለ ከተሞች በተደረጉ ጉብኝቶች የእህል ክምችትና አቅርቦቱ በቂ መሆኑን የአዲስ አባባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ቢኒያም ምክሩ አረጋግጠዋል፡፡

ከበዓላት ጋር ተያይዞም የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር ብሎም የአቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም ከክልሎች ጋር በቅንጅት እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

በገመቺስ ታሪኩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.