Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር እና ደሴ የከተሞቹን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የተለየያዩ ክልከላዎች ተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2 ፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር እና የደሴ ከተማ አስተዳደሮች የፀጥታ ኮማንድ ፖስቶች የከተሞቹን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ክልከላዎችን አስቀመጡ፡፡

የጎንደር ከተማ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ሚያዝያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ነው ክልከላዎችን ያሳለፈው፡፡

በዚህ መሰረትም ፡-

  1. በከተማው ያሉ ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች ከምሽቱ 3 ሰዓት በኋላ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው ፤

2 . በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ውጭ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ፣

3 .ከተፈቀደለት የመንግስት የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፣

4 . ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ ፣ ገጀራ ፣ አንካሴ ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፣

5 . በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ ፣ የደበቀ ፣ ሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያስመለጠ ፣ የፀጥታ ሃይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በህግ የተከለከለ ነው፣

6 . በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፣

7 . በተከለከሉ ቦታዎች በእምነት ተቋማት፣ በገበያዎች፣ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ፣ በሆቴሎች፣

መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎች፣ ልዩ ልዩ መዝናኛ ቦታዎች ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፣

8 . የሠራዊቱን ሚሊተሪ (አልባሳት) ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ የተከለከለ ነው፤ የልዩ ኋይል፣ የፖሊስ ፣ የመከላከያ ሠራዊት ፣ የፌዴራል ፖሊስ መልበስ የተከለከለ ነው፣

9 . ያልተፈቀዱ ስብሰባዎችን ማለትም ከመንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት የተከለከለ ነው፣

  1. አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ የተከለከለ ነው፣

11 . ፀጉረ ልውጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ እንዲሁም ለሚመለከተው የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል፣

በተመሳሳይ የደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማውን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል በዛሬው ዕለት ተሰብስቦ የሚከተሉትን ክልከላዎች አስቀምጧል፡፡

  1. ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ላልተወሰኑ ቀናት ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ፤
  2. በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:30 ሰዓት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ፤ እንዲሁም የሰው እንቅስቃሴ ከምሽቱ 4፡00 በኋላ የተከለከለ ነው።
  3. ከተፈቀደለት እና የፀጥታ ስምሪት ይዞ ከሚንቀሳቀሰው የመንግስት የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ክልክል ነው፡፡
  4. እንዲሁም ድምፅ አልባ እና ስለታማ የሆኑ መሣሪያዎችን ይዞ መንቀሳቀስ አይቻልም፡፡
  5. በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን መስጠት፣ መደበቅ፣ የፀጥታ ኃይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በህግ የተከለከለ ነው።
  6. በማንኛውም ቦታና ሰዓት ጥይትም ሆነ ርችት መተኮስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
  7. የሠራዊቱን የደንብ ልብስ ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ የተከለከለ ነው፡፡ የልዩ ኋይል፣ የፖሊስ፣ የመከላከያ ራዊት ፣ የፌዴራል ፖሊስ መልበስ የተከለከለ ነው።
  8. ከመንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት የተከለከለ ነው።
  9. አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
  10. ፀጉረ ልውጥ/አጠራጣሪ/ ሰው ከቤቱ ያሳደረ፣ ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዘ እንዲሁም ለሚመለከተው የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል።

ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ነዋሪው እንዲተባበር ኮማንድ ፖስቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.