Fana: At a Speed of Life!

ተቋማት ለገበታ ለትውልድ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውንቀጥለዋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የተለያዩ ተቋማት ድጋፍ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል፡፡
 
በ8ኛ ዙር የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትን ዝርዝር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ይፋ አድርጓል፡፡
 
ተቋማቱ ለፕሮጀክቱ ግንባታ የሚውል ከ5 ሚሊየን እስከ 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ነው የተገለጸው፡፡
 
በዚህ መሰረትም አርባ ምንጭ ቴክስታይል፣ አልፋራግ፣ አላይድ ኬሚካልስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ ራጅ አግሮ ኢንዱስትሪ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ ዌብስፕሪክስ አይቲ ሶሉሽን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ዳንጎቴ ሲሚንቶ ኢትዮጵያ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያና ሲኖማ ኢንተርናሽናል ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
 
በተጨማሪም ሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ባህራን ትሬዲንግ ፣ ዮቴክ፣ ጀርመን ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ፣ ሞቲ ኢንጅነሪንግ፣ ጎመጁ ኦይል፣ ገደብ ኢንጅነሪንግ፣ ንፋስ ስልክ ቀለም፣ ድሬ ብረታ ብረት፣ድሬዳዋ ራስ ሆቴልና ትራኮን ትሬዲንግ በ8ኛ ዙር ድጋፍ ማድረጋቸው ተመላክቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.