Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም እና ጉምሩክ ኮሚሽን የጋራ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም እና ጉምሩክ ኮሚሽን በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።

የአጋርነት ስምምነቱ የጉምሩክ ቀረጥ እና ታክስን በቴሌብር ሱፐር አፕ በመክፈል በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት አሰጣጥን መዘርጋት የሚያስችል ነው ተብሏል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ÷የኢትዮጵያን ጉምሩክ  የማዘመን ስራን በቴክኖሎጂ ማገዝ ምርጫ የሌለው መሆኑን ገልፀው ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የተደረገው ስምምነት ለዚህ አጋዥ ነው ብለዋል።

የጉምሩክ ቀረጥ እና ታክስን በቴሌብር መክፈል መቻሉ የጉምሩክ ገቢን በተሻለ ቅልጥፍና ለመሰብሰብ የሚጭበረበሩ የክፍያ  ደረሰኞቸን ለማስቀረት እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው ÷ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በጋራ እየተሰራ መሆኑ  አንስተው ከተቋማት ጋር የሚደረጉት የአጋርነት ስምምነቶች  ይህንኑ ተግባር እውን ለማድረግ አጋዥ ናቸው ብለዋል።

በሜሮን ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.