Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የወባ ስርጭትን ለመከላከል ሁሉን አቀፍ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በመጪው የክረምት ወቅት መግቢያ ሊከሰት የሚችለውን የወባ በሽታ ስርጭት ለመከላከል ሁሉን አቀፍ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ፡፡

በኢንስቲትዩቱ የወባ ማስወገድ ፕሮግራም አስተባባሪ ዳምጤ ላንክር÷ የዘንድሮ የወባ በሽታ ስርጭት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር ከፍ በማለቱ በቀጣይ ሦስት ወራት ሊከሰት የሚችለውን የወባ በሽታ ለመከላከል የድርጊት መርሐ ግብር ዕቅድ ተዘጋጅቷል ብለዋል።

በተጨማሪም በጥናት በተለዩ የምዕራብ አርማጭሆ፣ ቋራ፣ መተማ፣ ደራ፣ ፎገራ እና ጃዊ ወረዳዎች ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ የቤት ለቤት የፀረ ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ የተቀናጀ የወባ ማስወገድ ድጋፍና ክትትል የሚሠሩ ባለሙያዎችን የወባ ስጋት ወዳለባቸው ዞኖችና ወረዳዎች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በመላክ የድጋፍና ክትትል ሥራ እንደሚሠራ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

መጪው የክረምት ወቅት በመሆኑ ሕብረተሰቡ የወባ በሽታ መከላከያ ዘዴዎችን በመተግበር እየጨመረ ከመጣው የወባ በሽታ ስርጭት እራሱን እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.