Fana: At a Speed of Life!

የታሪካዊው የአውበርኸድሌ አዋች ዕድሳት ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በሐረሪ ክልል የሚገኘው የታሪካዊው የአውበርኸድሌ አዋች ዕድሳት ሥራ የማስጀመር መርሐ ግብር ተካሄደ።

የእድሳት ስራውን ያስጀመሩት የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪና የፌዴራል ቅርስና ጥበቃ ባለሥልጣን የሥራ ኃላፊዎች መሆናቸውን የሐረሪ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ለእንግዳ መቀበያና ለሙዝየምነት አገልግሎት ይውላል ተብሏል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በመርሐ-ግብሩ÷ መሰል ቅርሶችን በአግባቡ ተንከባክቦና ጠብቆ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው ቅርሶቹ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዲኖራቸውና ለቱሪስት መስህብነት እንዲውሉ ማስቻል ይገባል ብለዋል።

የአውበርኸድሌ አዋች መንደር ለረዥም ዓመታት ዕድሳት እንዳልተደረገለት ጠቅሰው በአጭር ጊዜ ሙሉ ዕድሳት በማድረግ አካባቢውን ለማልማት ይሠራል ብለዋል።

ከ1ሺህ ዓመት በላይ ያስቆጠረው የአውበርኸድሌ አዋች መንደር ቅርስ ለረዥም ዓመታት ዕድሳት እንዳልተደረገለት ጠቅሰው በአጭር ጊዜ ሙሉ ዕድሳት በማድረግ አካባቢውን ለማልማት ይሠራል ብለዋል።

በማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ ላይ ከሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በተጨማሪ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ነቢል ማኅዲ፣ የፌደራል ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.