Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ሐብት 1 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ሐብቱ 1 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር መድረሱን አስታወቀ።

ባንኩ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ123 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉንም አስታውቋል።

በተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ፣ ብድር በመስጠትና በመሰብሰብ፣ የዲጂታል ባንክ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ፣ በውጭ ምንዛሪ ግኝትና አቅርቦት እንዲሁም በሌሎች ፋይናንስና ፋይናንስ ነክ ባልሆኑ አፈፃፀሞች ውጤታማ ስራ መስራቱን ገልጿል።

የዲጂታል ባንክ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ባንኩ ወጤታማ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በዘጠኝ ወራት ውስጥ በዲጂታል ባንክ አማራጮች ብቻ 2 ነጥብ 1 ትሪሊየን ብር መንቀሳቀሱን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ባንኩ በቀጣይ በተለይ ዋና ዋና የትኩረት ዘርፎች በሆኑት በተቀማጭ ሃብት አሰባሰብ፣ በዲጂታል ባንክ አገልግሎት፣ በብድር አሰጣጥና አሰባሰብ፣ በውጭ ምንዛሪ ግኝት እንዲሁም የባንኩን የሪፎርም ስራዎች በማስቀጠል በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባው የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.