Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2015 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2015 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግን ለተከታታይ ሦስተኛ ጊዜ አሸንፏል።

በ25 ሳምንት የሊጉ መርሃግብር ይርጋጨፌ ቡናን የገጠመው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሎዛ አበራ ሃትሪክ እና በመሳይ ተመስገን አንድ ግብ 4 ለ 0 በመርታት አንድ ጨዋታዎች እየቀረው የሊጉ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 2004 ላይ ከተጀመረ ወዲህ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  የሊጉን ዋንጫ ለስድስተኛ ጊዜ ነው ያሸነፈው።

ንግድ ባንክ ዩጋንዳ በሚደረገው የሴካፋ  የሴቶች ክለቦች  ቻምፒዮንስ ሊግ ማጣርያ ውድድር ላይ እንደሚሳተፍም አረጋግጧል፡፡

አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት  እንደተናገሩት÷የውድድር አመቱ ፈታኝ እንደነበር እና በቀጣይ በአፍሪካ መድረክ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰሩ ተናግሯል።

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.