Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ መሐመድ በፋፈን ዞን ለሚገነባው የመንገድ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ በፋፈን ዞን በ45 ሚሊየን ብር ወጪ ለሚገነባው የቡላለሌ-አንተር-ሀረዋ የመንገድ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ።

በርዕሰ መስተዳድሩ  የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ልዑካን ቡድን በፋፈን ዞን ሀረዋ ወረዳ ጉብኝት አድርጓል፡፡

የሚገነባው የመንገድ ፕሮጀክት 16 ኪሎ  ሜትር  ርዝመት ያለው ሲሆን÷ ፕሮጀክቱ በክልሉ ቆላማ አካባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት  እንደሚገነባ  ተገልጿል።

አቶ ሙስጠፌ መሐመድ እና ልኡካን ቡድኑ ከሀረዋ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር በመሰረተ ልማት ችግሮችና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማካሄዱንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.