Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለፕሬዚዳንት ኤርዶኻን የደስታ መልዕክት ላኩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቱርክ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በድጋሚ ለተመረጡት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላለፉ።

ትናንት በቱርክ በተደረገ ምርጫ ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን በድጋሚ ተመርጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልዕክታቸው፥ “በድጋሚ በመመረጥዎ እንኳን ደስ ያልዎት” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የኢትዮጵያ እና ቱርክን ግንኙነት በቀጣይ የበለጠ ለማጠናከር በጋራ ለመሥራትም ዝግጁ መሆናቸውን ነው ያመላከቱት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.