Fana: At a Speed of Life!

በሐዋሳ ከወ/ሪት ፅጌ መጠለፍ ጋር በተያያዘ 6 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሞኑን በሐዋሳ ከተማ ወ/ሪት ፅጌ በላቸው የተባለች ወጣት በአንድ ግለሰብ የመጠለፏ ጉዳይ የማህበራዊ ሚዲያዎች አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል።

የከተማዋ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ዛሬ መግለጫ ያወጣ ሲሆን ፥ ከጠለፋ ወንጀሉ ጋር የተጠረጠሩ 6 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ነው ያስታወቀው።

የወንጀሉ ድሪጊት የተፈፀመው በሐዋሳ ከተማ በመናኸሪያ ክ/ከተማ መሆኑን የከተማው ፖሊስ ገልጿል፡፡

በዚህም ወ/ሪት ፅጌ በላቸው የተባለች ግለሰብ በቀን 15/9/2015 ዓ.ም ቤተሰቦቿ ተጠልፋ የት እንደደረሰች አናውቅም በማለት ለመነኸሪያ ክ/ከተማ ፖሊስ ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረት ምርመራ መጀመሩ ተገልጿል።

ይህን ተከትሎም መምሪያው ተፈፀመ ብሎ ባለው ወንጀል መሰረት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ብርቱ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝም ነው የጠቆመው፡፡

በዚህም ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ጭምር አስፈላጊውን ጥረት እያደረግኩ ነውም ብሏል፡፡

አክሎም በአንዳንድ ማህበራዊ የሚዲያ ተቋማት ከሚሰራጩ አሉባልታዎች የተበዳይ ቤተሰብም ሆነ ህዝቡ ሳይደናገር እንዲጠብቅና ለፖሊስ መረጃ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

በዚህም ከወ/ሪት ፅጌ በላቸው የጠለፋ ወንጀል ጋር የተጠረጠሩ ሥድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም ተጠርጣሪው ሣጅን የኋላ መብራቴ እና የተጠለፈችውን ወ/ሪት ፅጌ በላቸው ይዞ ከተሰወረበት ቦታ አድኖ ለመያዝ ጥረትና ክትትል እየተደረገ ነውም ብሏል ፖሊስ።

ህብረተሰቡ የሚችለውን ሁሉ በ09 64 50 46 77 እና 09 69 41 52 72 ስልክ ቁጥሮች ጥቆማ እንዲሰጥ የከተማዋ ፖሊስ ጠይቋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.