Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለ3ኛ ጊዜ አሰልጣኙን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለሦስተኛ ጊዜ አሰልጣኙን አሰናብቷል፡፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ2011 ከፕሪምየር ሊጉ ከወረደ በኋላ ነበር በያዝነው ዓመት ዳግም መመለስ የቻለው።

ክለቡ ከታችኛው የሊግ ዕርከን ካሳደገው አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ጋር ለ7 የሊግ ጨዋታዎች ከቆየ በኋላ በምትኩ ለረዳት አሰልጣኙ ገዛኸኝ ከተማ ኃላፊነት በመስጠት እስከ 2ኛው ዙር የመጀመሪያ ሳምንታት ድረስ ቢቆይም ለሁለተኛ ጊዜ አሰልጣኙን በማሰናበት አሰልጣኝ ስምዖን አባይን በቦታው ሾሞ ነበር፡፡

ክለቡ እስከ 26ኛ ሳምንት ድረስ በአሰልጣኙ ሲመራ ቆይቶ ÷ አሰልጣኝ ስምዖንን ከኃላፊነት በማንሳት በምትካቸው የግብ ጠባቂ አሰልጣኙ ቅጣው ሙሉን ቀጣይ የመጨረሻ አራት ጨዋታዎችን እንዲመራ መሾሙን የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ለማ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሳምንታት በፊት ወደ አስር የሚደርሱ ተጫዋቾቹን ወጪ ለመቀነስ በማሰብ ማሰናበቱንም ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.