Fana: At a Speed of Life!

የኢንዱስትሪ ፓርኮች በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር እየተሰራ ነው – ኮርፖሬሽኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከርና ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ።

የኮርፖሬሽኑ የኮሙኒኬሽን ሃላፊ ዘመን ጆንድ÷ ኮርፖሬሽኑ የሀገሪቱን መዋቅራዊ ሽግግር እውን ለማድረግ ከመስራት ጎን ለጎን ለአካባቢ ጥበቃና ሥነ-ምህዳር መጠበቅ የራሱን አበርክቶ እየተወጣ ነው ብለዋል።

ባለፉት አራት ዓመታት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ከ2 ሚሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸውን አስታውሰዋል።

ችግኞቹ ተገቢው ጥበቃና እንክብካቤ ሲደረግላቸው የቆየ መሆኑን ጠቁመው÷ የፅድቀት መጠናቸውም ከ90 በመቶ በላይ መሆኑን አስረድተዋል።

ኮርፖሬሽኑ በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ከ1 ሚሊየን በላይ የተለያዩ ዝርያ ያላቸውን የዛፍ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቀጣይም የኢንዱስትሪ ፓርኮች በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከርና ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ነው የገለጹት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.