Fana: At a Speed of Life!

በአለም በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ200 ሺህ አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 18፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በአለም በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ200 ሺህ ማለፉ ተገለጸ።

እንደ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት በአለም በኮቪድ-19 ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ200 ሺህ በልጧል።

በአለም በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ከ2 ሚሊዮን 921 ሺህ በላይ መመዝገቡ ነው መረጃው የሚያሳየው።

መረጃው እንደሚያሳየው ወረርሸኙ እስካሁን የ203 ሺህ 289 ሰዎች ሕይወት እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል፡፡

ከ50 ሺህ በላይ የሚሆነው ሞት የተመዘገበውም በአሜሪካ ነው፡፡

ከአሜሪካ በተጨማሪ ጣሊያን፣ ስፔን፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ እያንዳንዳቸው ከ20 ሺህ በላይ ዜጎቻቸውን በቫይረሱ ተነጥቀዋል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በአፍሪካ፣ በምስራቅ አውሮፓ ፣ በማዕከላዊና ደቡብ አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍ ሊል እንደሚችል ማስጠንቀቃቸው የሚታወስ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ ሃገራት የእንቅስቃሴ ገደቦችን ማንሳት ተከትሎ ዋና ዳይሬክተሩ ቫይረሱ እንዲያገረሽ ያደርጋል ማለታቸው ይታወሰዋል፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.