Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 2ኛው ዙር የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ መካሄድ ጀምሯል።

የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን ባዘጋጀው ውድድር ከስድስት ክለቦች የተውጣጡ ከ90 በላይ ስፖርተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

ውድድሩ በአዋቂዎችና በታዳጊዎች በሁለቱም ፆታ የሚካሄድ ሲሆን÷በቀጣይ በቱኒዚያ ለሚካሄደው የአፍሪካ ጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ የተሻሉ ስፖርተኞችን ለመምረጥ እንደተዘጋጀ ተጠቅሷል፡፡

ውድድሩ እስከ አርብ ሰኔ 02 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚቆይ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.