የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ ተከላ ሲገባደድ ኢትዮጵያ 31 ቢሊየን ችግኝ ትለብሳለች – ጠ/ሚ ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ ተከላ ሲገባደድ ኢትዮጵያ 31 ቢሊየን ችግኝ ትለብሳለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ “የጀመርነውን እንጨርሳለን፤የዘንድሮን የአረንጓዴ ዐሻራ ተከላ ስናገባድድ ኢትዮጵያ በ31 ቢሊየን ችግኝ ትለብሳለች” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኑ ይህንን ታሪክ አብረን እንሥራ” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሁለተኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐግ ብር በትናንትናው ዕለት በአፋር ክልል በይፋ ማስጀመራቸው ይታወቃል፡፡