Fana: At a Speed of Life!

“ንግድዎን በመቅረዝ ላይ ያኑሩ” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ አውደ ርዕይ እና ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ንግድዎን በመቅረዝ ላይ ያኑሩ” በሚል መሪ ቃል ፊንቴክስ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች፣ የቤተ ውበት እና የግንባታ አጨራረስ ምርቶች፣ አገልግሎቶች እና ቴክኖሎጂዎች ዓለም አቀፍ አውደ ርዕይ እና ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

አውደ ርዕዩ እና ኮንፈረንሱ ከሰኔ 8 እስከ ሰኔ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በሚሊኒየም አዳራሽ ነው ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄደው።

አውደ ርዕዩን እና ኮንፈረንሱን ፕራና ኤቨንትስ እና አፍሪካን ትረስትድ ፓርትነርስ በጋራ አዘጋጅተውታል።

ፊንቴክስ ዘላቂ የንግድ ትስስርን ለመፍጠር እና እድገትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ዓውደ-ርዕይ ሲሆን ለተሳታፊዎች የንግድ ስኬት የሚተጋ እና የንግዱን ማህበረሰብ ትኩረት በመሳብ በቦታው ላይ ለሚደረጉ የግብይት ውሳኔዎች ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል።

በአውደ-ርዕዩ በርካታ የሀገር ውስጥ አምራች ኩባንያዎች የሚሳተፉ ሲሆን ከ400 በላይ ገዢዎች እንዲሁም ከ4 ሺህ በላይ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት እና ጎብኚዎች እንደሚስተናገዱበት ይጠበቃል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.