Fana: At a Speed of Life!

ዋሊያዎቹ ከማላዊ ጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ዝግጀት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አምስተኛ የምድብ ጨዋታ ዝግጅቱ ጀምሯል።

ብሄራዊ ቡድኑ በዛሬው ዕለት የመጀመሪያ ቀን ልምምዱን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ማከናወኑ ተገልጿል፡፡

በዛሬው ልምምድ መርሐ ግብር ላይ 17 ተጫዋቾች የተገኙ ሲሆን÷ ቀሪዎቹ አምስት ተጫዋቾች ቡድኑን በመቀላቀል ከነገ ጀምሮ ልምምድ የሚያከናውኑ ይሆናል።

ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ የተደረገላቸው 23 ተጫዋቾች ዝርዝር ቅዳሜ ምሽት ይፋ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከማላዊ ጋር የሚያደርገውን አምስተኛ የምድብ ጨዋታ ሞዛምቢክ ላይ በቀጣይ ሳምንት የፊታችን ሰኔ 13 ቀን እንደሚያከናውን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.