Fana: At a Speed of Life!

አቶ ጌታቸው ሀጎስ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ጊዜያዊ ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ጌታቸው ሀጎስ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ጊዜያዊ ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን ተሾሙ።
ከ20 ዓመት በላይ የኩባንያዎቹ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ያገለገሉት ዶክተር አረጋ ይርዳው ከሃላፊነት መነሳታቸውን ተከትሎ ነው የተሾሙት።
 
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሊቀመንበር መሀመድ አል አሙዲ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ እንደሚጠቁመው አቶ ጌታቸው ሀጎስ የሚድሮክ ኢትዮጵያ እህትና ተባባሪ ኩባንያዎችም ከሚያዚያ 17 ቀን 2012 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ጊዜያዊ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ለተሾሙት አቶ ጌታቸው ሀጎስ ተገቢውን ትብብር እንዲያደርጉ ይጠይቃል።
 
80 የሚድሮክ ኢትዮጵያ እህትና ተባባሪ ኩባንያዎች ያሉ ሲሆን፥ እነዚህም ኩባንያዎች በግብርና፣ በአግሮ ኢንዱስትሪ፣ በግንባታ፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ በማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ በማእድን ልማት፣ በነዳጅና ጋዝ፣ በሪል ስቴት፣ በንግድ፣ በጤና፣ በትምህርትና ስልጠና ዘርፎች ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.