Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ለ291 ፕሮጀክቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ291 ፕሮጀክቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ፡፡

ፈቃዱ የተሰጠው÷ በግብርና ለ120 ፕሮጀክቶች፣ በአገልግሎት ለ89 እና በኢንዱስትሪ ለ82 ፕሮጀክቶች መሆኑ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በግብርና፣ በአገልግሎት እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ከ12 ቢሊየን 852 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል መመዝገቡን የቢሮው ኃላፊ ሃልጌዮ ጅሎ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

ከ2 ቢሊየን 266 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 25 ዳያስፖራዎች ከ1 ሺህ 853 ሄክታር በላይ በምደባ እንዲተላለፍላቸው ተወስኗል ብለዋል፡፡

345 አዳዲስ ፋይሎች መመዝገባቸውንም ነው ኃላፊው ያነሱት፡፡

የገጠር ኢንቨስትመንት መሬት ዝግጅትን በተመለከተም÷ ከ26 ሺህ 600 ሄክታር በላይ ስለመዘጋጀቱ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በተገባው ውል መሰረት ማልማት ባልቻሉ 52 ፕሮጀክቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ነው ኃላፊው የገለጹት፡፡

በየሻምበል ምህረት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.