Fana: At a Speed of Life!

6ኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ዓመታዊ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ዓመታዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የቀጣናው የፋይናንስ ዘርፍ አቅም፣ ቀጣናዊ ትስስር፣ የፋይናንስ አቅርቦትና ተደራሽነት፣ የፋይናንስ ዘርፍ ውጤቶች አፈጻጸም፣ ልምዶች፣ የዘርፉ እድሎች እና ተግዳሮቶች ውይይት እንደሚደረግባቸው ተገልጿል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባኤ የመድን፣ የማይክሮ ፋይናንስ፣ የባንክ እና ሌሎች የፋይናንስ ዘርፍ ተቋማት ተወካዮችና ዓለም አቀፍ የሒሳብ ባለሙያዎች እንደሚሳተፉ ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.