Fana: At a Speed of Life!

በኦስሎ ዳይመንድ ሊግ የአንድ ማይል ውድድር  ብርቄ ሃየሎም የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኖርዌይ ኦስሎ ዳይመንድ ሊግ የአንድ ማይል ውድድር ብርቄ ሃየሎም የዓለም ከ20 ዓመት በታች ክብረ ወሰን በመስበር አሸንፋለች፡፡

አትሌት ብርቄ ርቀቱን በ4 ደቂቃ 17 ሰከንድ 13 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው የዓለም ከ20 ዓመት በታች ክብረወሰን በመስበር ያሸነፈችው፡፡

በውድድሩ ወርቅነሽ መለሰ 5ኛ ፣ ሂሩት መሸሻ 7ኛ ፣ አክሱማይት አምባዬ ደግሞ 12ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ደግሞ ዮሚፍ ቀጀልቻ የውድድር ዘመኑን እና የግሉን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል።

ዮሚፍ ውድድሩን በ12 ደቂቃ 41 ሰከንድ 73 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ ያሸነፈ ሲሆን÷ የገባበት ሰዓት የግሉ ፈጣን ሰዓት፤ ከዓለም ደግሞ 5ኛው ምርጥ ሰዓት በመሆን ተመዝግቧል።

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ጥላሁን ሃይሌ ውድድሩን 3ኛ በመሆን ሲያጠናቅቅ ሳሙኤል ተፈራ ደግሞ 7ኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቁን ከኦስሎ ዳይመንድ ሊግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.