Fana: At a Speed of Life!

ከ141 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሰኔ 2 እስከ 8 ቀን 2015 ዓ.ም በተደረገ ክትትል 141 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በተጨማሪም የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ስድስት ግለሰቦች እና አራት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙት በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች መሆኑን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር የላቀ አፈጻጸም የተመዘገበ ሲሆን÷ ጅግጅጋ፣ ሞያሌ እና አዋሽ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በቅደም ተከተላቸው 21 ሚሊየን፣ 18 ሚሊየን እና 11 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በመያዝ ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል ብሏል ኮሚሽኑ፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ ነው የተያዙት፡፡

ከተያዙት ዕቃዎች መካከል÷ አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድኃኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.