Fana: At a Speed of Life!

ቼልሲ ንኩንኩን ሲያስፈርም አርሰናል ለራይስ 90 ሚሊየን ፓውንድ አቅርቧል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የአውሮፓ ክለቦች በቀጣዩ ዓመት ተጠናክረው ለመቅረብ በተጫዋቾች ዝውውር በስፋት እየተሳተፉ ነው።

በተለይም የዝውውር መስኮቱ የተከፈተላቸው የእንግሊዝ ክለቦች ራሳቸውን እያጠናከሩ ሲሆን÷ በዚህም ቼልሲ ፈረንሳዊውን አጥቂ ክርስቶፈር ንኩንኩን ከአር ቢ ሌፕዚግ አስፈርሟል።

ንኩንኩ ክለቡን ለተረከቡት አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ የመጀመሪያው ፈራሚ በመሆን ÷ በ52 ሚሊየን ፓውንድ ምዕራብ ለንደን ደርሷል።

በሌሎች የዝውውር ጭምጭምታዎች የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ለካይ ሃቨርትዝ እና ጁሪዬን ቲምበር የዝውውር ጥያቄ ማቅረቡ ተሰምቷል።

አሰልጣኝ አርቴታ ለጀርመናዊው ሃቨርትዝ 60 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ገንዘብ አቅርቧል ነው የተባለው።

በተጨማሪም ለተጫዋቹ የ210 ሺህ ፓውንድ ሳምንታዊ ደመወዝ ለመክፈል መዘጋጀቱንም ዘገባዎች ያመላክታሉ።

ለአያክሱ ተከላካይ ቲምበርም 30 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፥ ክለቡ ግን ጥያቄውን ውድቅ አድርጎበታል።

ምናልባት የተሻሻለ ክፍያ ካቀረበ ተጫዋቹን የግሉ ሊያደርገው እንደሚችል ስካይ ስፖርት አስነብቧል።

በተያያዘም አርቴታ እንግሊዛዊውን የዌስትሃም ዩናይትድ አማካይ ዴክላን ራይስን የግሉ ለማድረግ በ90 ሚሊየን ፓውንድ የክለቡ ክብረወሰን የሆነ የዝውውር ገንዘብ ማቅረቡ ተሰምቷል።

ለዝውውር በርካታ ገንዘብ ያወጣው ቼልሲ ደግሞ የብራይተኑን አማካይ ካይሴዶን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምሯል።
ይሁን እንጅ ክለቡ ተጫዋቹን የግሉ ለማድረግ በርካታ ተጫዋቾችን በቅድሚያ ማሰናበት ይኖርበታል ነው የተባለው።

የክለቡ የሽያጭ ጉዳይ ያልለየለት የላንክሻየሩ ማንቼስተር ዩናይትድ አሁንም ስሙ ከበርካታ ተጫዋቾች ጋር ቢያያዝም የገፋ የዝውውር ጥያቄ ያቀረበው ለእንግሊዛዊው አማካይ ማሰን ማውንት ብቻ ነው።

ክለቡ ለቼልሲው አማካይ ያቀረበው የዝውውር ገንዘብ ውድቅ የተደረገበት ሲሆን፥ አሰልጣኝ ቴን ሃግ አማካይና አጥቂን ጨምሮ የመሃል ተከላካይና ግብ ጠባቂ እንደሚፈልጉ ሲናገሩ ቆይተዋል።

በኒውካስትልና ስቶክ ያልተሳካ ጊዜን ያሳለፈው ጆሴሉ የስፔኑን ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪድን ተቀላቅሏል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.