Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ጨዋታ እየቀረው የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሀድያ ሆሳዕና ያገናኘው የ29ኛ ሳምንት ጨዋታ÷ 9፡00 ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በጨዋታውም÷ ቸርነት ጉግሳ በመጀመሪያው አጋማሽ እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚውን ረትቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.