Fana: At a Speed of Life!

በሀዲያ ዞን ሾኔ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ሾኔ ከተማ አስተዳደር በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከል መረጃና ስታቲክስ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ታምራት ደሳለኝ÷ አደጋው በሾኔ ከተማ አስተዳደር ማዞሪያ ቀበሌ ሌሊት 11 ሰዓት 40 ላይ መከሰቱን ገልጸዋል፡፡

ከወላይታ ሶዶ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ ፒካፕ ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ከሚጓዝ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ጋር ተጋጭቶ በውስጡ የነበሩ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላት እና አንድ ጎረቤት በድምሩ የአራት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

በሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሟቾቹ መካከል ምጥ ይዟት ወደ ሆስፒታል እያመራች የነበረች እናት እንደምትገኝበት የገለጹት ኢንስፔክተር ታምራት÷ የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.