Fana: At a Speed of Life!

ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ25 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ25 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ፡፡

አገልግሎቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለመሰብሰብ ካቀደው 27 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ውስጥ 25 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታውቋል።

በዚህም የዕቅዱን 93 በመቶ ማሳካት የተቻለ ሲሆን÷ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ4 ነጥብ 665 ቢሊየን ብር ብልጫ ማሳየቱ ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.