Fana: At a Speed of Life!

በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ አትሌቶች መወዳደር የሚችሉባቸው እና የተከለከሉባቸው ርቀቶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች መወዳደር የሚችሉባቸው እና የተከለከሉባቸው ርቀቶች ይፋ ሆኑ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በመጪው ነሐሤ ወር በሃንጋሪ በሚካሄደው የዓለም ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፉ አትሌቶችን ቀጣይ የውድድር ቀን ላይ ቀነ ገደብ አስቀምጧል።

ከነሐሤ 13 እስከ 21 ቀን በሃንጋሪ ቡዳፔስት በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፉ አትሌቶች በውድድሮች ላይ እየተሳተፉ መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገልጿል፡፡

በዚህም ምክንያት የተከለከሉ እና ፍቃድ የተሰጣቸው ርቀቶችን ለይቶ አስታውቋል።

በ5 ሺህ ሜትር እና በ3ሺህ ሜትር መሰናክል በሁለቱም ጾታዎች ፣ እንዲሁም በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የተመረጡ አትሌቶች ከነገ ሐምሌ 8 ቀን ጀምሮ መወዳደር አይችሉም ብሏል።

በተጨማሪም በ800 ሜትር በሁለቱም ፆታዎች በ1 ሺህ 500 ሜትር ወንዶች እስከ ሐምሌ 17 ቀን ድረስ በተመረጡበት ርቀቶች ብቻ መወዳደር ይችላሉ ተብሏል።

ከዚህ ውጪ ማንኛውም አትሌት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሀገራት ውድድሮች ላይ መሳተፍ እንደማይችልም ነው የገለጸው።

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.