Fana: At a Speed of Life!

በፖላንድ የዳይመንድ ሊግ አትሌት ሂሩት መሸሻ እና ፍሬወይኒ ሀይሉ አሸነፉ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዳይመንድ ሊግ 8ኛ ከተማ በሆነችው የፖላንዷ ሲሌሲያ ከተማ በተደረገ ውድድር አትሌት ሂሩት መሸሻ እና ፍሬወይኒ ሀይሉ ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በ1 ሺህ 500 ሜትር በተደረገ ውድድር በሴቶች ሂሩት መሸሻ 3 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ በመግባት ስታሸንፍ በርቀቱ የግሏን ምርጥ ሰዓት ማስመዝገብ ችላለች፡፡

ብርቄ አየሎም 2ኛ፣ድርቤ ወልተጂ 3ኛ እንዲሁም ወርቅነሽ መለሰ 4ኛ ደረጃ በመያዝ እና የየግል ፈጣን ሰዓታቸውን በማስመዝገብ ርቀቱን አጠናቅቀዋል ።

በ3 ሺህ ሜትር በተደረገ ሌላ ውድድር ደግሞ አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ የውድድር ቦታውን አዲስ ክብረወሰን በማስመዝገብ አሸንፋለች ።

ፍሬወይኒ ሀይሉ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 8 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ የወሰደባት ሲሆን÷ በዚሁ ርቀት አትሌት ለምለም ሀይሉ የግል ምርጥ ሰዓቷን በማሻሻል 3ኛ ወጥታለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.