Fana: At a Speed of Life!

ቤንጃሚን ሜንዲ ዳግም ወደ እግር ኳስ ተመልሷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የማንቼስተር ሲቲ ተካላካይ ቤንጃሚን ሜንዲ ከፍርድቤት እንግልት በኋላ ዳግም ወደ እግር ኳስ ተመልሷል፡፡

በዚህ ክረምት ወር ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ያለው ኮንትራት የተጠናቀቀው ሜንዲ ከቀናት በፊት በፈረንሳይ ሊግ ዋን ለሚገኘው ሎሬንት ክለብ መፈረሙ ተሰምቷል፡፡

የ29 ዓመቱ የግራ ተከላካይ ቤንጃሚን ሜንዲ ከአስገድዶ መድፈር ጋር በተያያዘ ለበርካታ ጊዜ ከእግርኳስ ርቆ የነበረ ሲሆን ባለፈው ዓርብ በፍርድ ቤት ከተጠረጠረበት ወንጀል ነፃ መባሉ የሚታወስ ነው፡፡

ፈረንሳዊው ተከላካይ በ2017 የአለማችን ውዱ ተከላካይ በመሆን ከሞናኮ ወደ ማንቼስተር ሲቲ በ52 ሚሊየን ፓውንድ መፈረሙ ይታወሳል።

ሜንዲ ባለፈው ጥር ወር ስድስት አስገድዶ መድፈር እና የፆታዊ ጥቃት ወንጀሎች ክስ ተመስርቶበት የነበረ ሲሆን በእንግሊዙ ቼስተር ከተማ ፍርድ ቤት ነፃ መባሉን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡

ሜንዲ ከሲቲ ጋር የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ያነሳ ሲሆን፥ በሩሲያ አስተናጋጅነት የተካሄደውን የዓለም ዋንጫ ያነሳው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አባልም ነበር።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.