Fana: At a Speed of Life!

በሴካፋ ከ18 ዓመት በታች የሴቶች የእግር ኳስ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በሴካፋ ከ18 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዩጋንዳ አቻው 1 ለ 0 ተሸንፏል።
በምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ማኅበራት ምክር ቤት(ሴካፋ) ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው ከ18 ዓመት በታች ውድድር ዛሬ በታንዛንያ ዳሬ ሰላም ተጀምሯል።
10 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዩጋንዳ አለንስ ናሳዚ በ68ኛው ደቂቃ ባስቆጠረችው ግብ ኢትዮጵያን 1 ለ 0 አሸንፋለች።
በአሰልጣኝ እንዳልካቸው ጫካ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ ጨዋታውን ከነገ በስቲያ ከውድድሩ አስተናጋጅ ታንዛኒያ ጋር ያደርጋል።
ቀን በተካሄደው የውድድሩ መክፈቻ ጨዋታ አስተናጋጇ ሀገር ታንዛንያን ብሩንዲን 3 ለ 0 ማሸነፏንም ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.