Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከ57 ሺህ በላይ ታዳጊዎች የስፖርት ስልጠና እየወሰዱ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከ57 ሺህ በላይ የሆኑ ታዳጊዎች በክረምት የስፖርት ስልጠና መርሀ ግብር እየተሳተፉ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
በሁለቱም ፆታዎች ዕድሜያቸው ከ9 እስከ 17 ዓመት የሆኑ ታዳጊዎች በስልጠናው እየተሳተፉ መሆኑ ተገልጿል።
ሰልጣኞቹ በ23 የስፖርት ዓይነቶች በየዝንባሌያቸው ስልጠናውን እየወሰዱ መሆኑን በቢሮው የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክተር አቶ ጎሳየ አለማየሁ የተናገሩት።
በከተማዋ በሚገኙ አራት ኪሎ፣ ራስ ሀይሉ፣ ጃን ሜዳ፣ አበበ ቢቂላ እና የአዲስ አበባ ቴኒስ ትምህርትና ስልጠና ማዕከላት ስልጠናው እየተሰጠ እንደሚገኝም ነው የገለጹት፡፡
ማዕከላቱ በክረምት ከሚያሰለጥኗቸው ሰልጣኞች በየስፖርት ዓይነቱ በመመልመል ልዩ ስልጠና እንዲወስዱ እንደተደረገ መናገራቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.