Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የክለቦች ውድድር መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2016 የክለቦች የውድድር መርሐ ግብር ይፋ ሆኗል።

በዚህ መሠረት ፕሪሚየርሊጉ ኢትዮጵያ መድን ከባህርዳር ከተማ በሚያደርጉት ጨዋታ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም ጅማሮውን ያደርጋል፡፡

በመጀመሪያው ሳምንት  ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና፣ አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ሻሸመኔ ከተማ ከወላይታ ድቻ፣ ሀምበሪቾ ዱራሜ ከድሬዳዋ ከተማ፣ ሀዋሳ ከተማ ከፋሲል ከነማ፣ ሀድያ ሆሳዕና ከመቻል እንዲሁም  ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወልቂጤ ከተማ ጨዋታቸውን  ያደርጋሉ፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና  መካከል የሚደረገው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ደግሞ በሰባተኛ ሳምንት ይደረጋል ።

በተያያዘ የ2015 የኢትዮጵያ ፕሪሚርሊግ የኮከቦች ሽልማት እና የክለቦች የገንዘብ ሽልማት ነሃሴ 13 በሀያት ሬጀንሲ ሆቴል የሚካሄድ መሆኑን ሊግ ኩባንያው አስታውቋል፡፡

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.