Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲና በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ መራዘም ዙሪያ መግባባት ላይ ደረሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ መራዘም ዙሪያ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገለፀ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በኮቪድ-19 እና በምርጫ መራዘም በዛሬው እለት ውይይት ማካሄዱን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

በውይይቱ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ቤኒሻንጉል ህዝብ ነፃነት ንቅናቄ ለሰላምና ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ቤህነን ሰዴድ)፣ የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) እና ቦሮ ዴሞክራሲያ ፓርቲ(ቦዴፓ) ተሳትፈዋል።

በውይይታቸውም የምርጫው መራዘም ትክክለኛ ዕርምጃ መሆኑ ላይ የተግባቡት ፓርቲዎቹ፣ በቀረቡ የህግ አማራጮቹም ላይ መግባባት ላይ ደርሰዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በቀጣይም በልማት፣ በሰላም እና ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ደርሰዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.