Fana: At a Speed of Life!

በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሚሳተፉ አትሌቶች ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሚወክሉ አትሌቶች ሽኝት ተደርጓል፡፡

19ኛው የዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ከነሐሴ 13 እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም በሀንጋሪ ቡዳፔስት ከተማ ይካሄዳል።

በሽኝት መርሐ ግብ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ተገኝተዋል፡፡

ልዑኩ ዛሬ ምሽት የሚያቀናውን የዓለም አትሌቲክስ የኮንግረስ አባላት ጨምሮ በሰባት ዙር ተከፍሎ ወደ ሀንጋሪ እንደሚያመራ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል::

አራት አትሌቶችን የያዘው የመጀመሪያው የስፖርተኞች ቡድን ማክሰኞ ወደ ስፍራው ያቀናል ተብሏል፡፡

የፊታችን ረቡዕ ድግሞ በ10 ሺህ እና በ1ሺህ 500 ሜትር በሴቶች እንዲሁም በወንዶች 3 ሺህ መሰናክል ተሳታፊዎችን የያዘው ቡድን ወደ ቡዳፔስት እንደሚጓዝ ተገልጿል፡፡

ቅዳሜ በሚጀመረው ውድድር ኢትዮጵያ በ19 ሴቶች እና በ16 ወንዶች በአጠቃላይ በ35 አትሌቶች ትወከላለች፡፡

በታሪኩ ጉታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.