Fana: At a Speed of Life!

2ተኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ሀንጋሪ ቡዳፔስት ገብቷል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ19ኛው የዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና  የሚሳተፈው የኢትየጵያ አትሌቲክስ 2ተኛው ልዑክ ከደቂቃዎች በፊት ሀንጋሪ ቡዳፔስት ገብቷል፡፡

በልዑካን ቡድኑ ውስጥ የሜዳሊያ ተጠባቂዎቹን ሰለሞን ባረጋ እና በሪሁ አረጋዊን ጨምሮ ሌሎች አትሌቶች እና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አመራሮች ተካትተዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት ቡዳፔስት ከተማ በመገኘት የተሳታፊነት ማረጋገጫ ካርድ መውሰዳቸውንም  የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ቀደም ሲል በርካታ አትሌቶችን እና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮችን ያቀፈው የመጀመሪያ ተጓዦች ልዑክ ሀንጋሪ ቡዳፔስት መግባቱ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.