Fana: At a Speed of Life!

ቲዎ ዋልኮት ከእግር ኳስ ተጫዋችነት ራሱን አገለለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአርሰናል እና የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን የክንፍ ተጫዋች ቲዎ ዋልኮት በ34 ዓመቱ ከፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋችነት ራሱን አግልሏል፡፡

ዋልኮት ለልጅነት ክለቡ አርሰናል ከ100 በላይ ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን በእግር ኳስ ህይወቱ 47 የእንግሊዝ ብህራዊ ቡድን ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል፡፡

በ16 ዓመቱ አርሴናልን የተቀላቀለው ዋልኮት ሶስት የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን እና ሁለት የኮሚዩኒቲ ሽልድ ዋንጫዎችን ጨምሮ ሌሎች ክብሮችንም ማሳካት ችሏል፡፡

ዋልኮት በፈረንጆቹ 2006 በነበረው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ስብሰብ ውስጥ አባል የነበረ ሲሆን እንግሊዝ ከሀንጋሪ ጋር ባደረገችው ጨዋታ በ17 ዓመቱ በመሰልፍ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን በእድሜ ትንሹ ተጫዋች መሆን ችሎ ነበር፡፡

በአጠቃላይ በተለያዩ ክለቦች 563 ጊዜ መሰለፍ የቻለው ዋልኮት በ34 ዓመቱ ከፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋችነት ራሱን ማግለሉን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ማስታወቁን ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.