Fana: At a Speed of Life!

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ እድገት ላበረከተችው አስተዋፅኦ እውቅና ተሰጣት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ እድገት ላበረከተችው አስተዋፅኦ የ”ፕላክ ኦፍ ሜሪት” ሽልማት እና እውቅና ተበርክቶላታል፡፡

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ በአትሌቲክስ ዘርፍ የኢትዮጵያን ስም በዓለም አደባባይ ያስጠራች ድንቅ አትሌት ስትሆን÷ አሁን ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በመሆን እያገለገለች ትገኛለች፡፡

ደራርቱ በአትሌቲክሱ ዘርፍ እስካሁን ላበረከተችው አስተዋፅኦም የዓለም አትሌቲክስ ኮንግረስ የ”ፕላክ ኦፍ ሜሪት” ሽልማት እና እውቅና እንደሰጣት የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ በሀንጋሪ በሚካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመሳተፍ ከኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ጋር ከቀናት በፊት ቡዳፔስት መግባቷ ይታወሳል፡፡

የ”ፕላክ ኦፍ ሜሪት” ሽልማት በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ኮንግረስ በአትሌቲክስ ዘርፍ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሰዎች የሚሰጥ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.