Fana: At a Speed of Life!

19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በቡዳፔስት ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሀንጋሪ ቡዳፔስት በዛሬው ዕለት ይጀመራል፡፡
በውድድሩ የመጀመሪያ ቀን በ3 ሺህ ሜትር መሠናክል ወንዶች ማጣሪያ ለሜቻ ግርማ፣ ጌትነት ዋለ እና አብርሃም ስሜ ኢትዮጵያን ወክለው ይሳተፋሉ፡፡
በተጨማሪም በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ሒሩት መሸሻ፣ ብርቄ ሃየሎም እና ድርቤ ወልተጂ በውድድሩ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡
በሌላ በኩል በ1 ሺህ 500 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ታደሰ ለሚ፣ ሳሙኤል አባተ እና አዲሱ ግርማ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ፡፡

ምሽቱ 3 ሰዓት ከ55 ላይ ደግሞ በ10 ሺህ ሜትር የሴቶች የፍጻሜ ውድድር ለተሰንበት ግደይ፣ ጉዳፍ ፀጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና ለምለም ኃይሉ ኢትዮጵያን ወክለው እንደሚሳተፉ የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.