Fana: At a Speed of Life!

በ 3 ሺህ ሜትር መሰናክል የወንዶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ በሚገኘው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ 3 ሺህ ሜትር መሰናክል የወንዶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜ አለፉ።

በምድብ አንድ የተወዳደረው አትሌት ጌትነት ዋለ 8:19.99 በሆነ ሰዓት በመግባት ከምድቡ 1ኛ በመውጣት ወደ ፍፃሜ ውድድር ማለፍ ችሏል።

በምድብ ሶስት የተወዳደረው አትሌት ለሜቻ ግርማ ለሜቻ ግርማ በ 8:15.89 ሰዓት 1ኛ በመውጣት ወደ ፍፃሜ ውድድር ማለፍ ችሏል።

በምድብ ሁለት የተወዳደረው አትሌት አብርሃም ስሜ በ 8:31.49 ሰዓት 8ኛ በመውጣት ወደ ፍፃሜው ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.