Fana: At a Speed of Life!

የ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የምትካፈልበት የ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ውድድር ምሽት 2 ሰዓት ላይ ይካሄዳል፡፡

በሀንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ የሚገኘው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ስድስተኛው ቀኑን ይዟል፡፡

በዛሬው እለትም የ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ማጣሪያ ውድድር ምሽት 2 ሰዓት ላይ የሚካሄድ ሲሆን÷ ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ሀጐስ ገ/ሕይወት እና በሪሁ አረጋዊ ኢትዮጵያን ወክለው እንደሚሳተፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.