Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ የዘጠኝ ወር እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ፣ግንቦት1፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በዘርፍ የዘጠኝ ወር እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሂዷል።

ሚኒስቴሩ ውይይቱን ከክልሎች እና ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር  በቪድዮ ኮንፍረስ  ያካሄደ ሲሆን÷በውይይቱም በእቅድ አፈጻጸም ወቅት የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች መዳሰሳቸው ተገልጿል።

ከዚያም ባለፈ በውይይቱ በቀጣይነት ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ሥራዎች ላይ  ትኩረት ተደርጓል ተብሏል።

በዚሁ ወቅት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር  ኢንጂነር አይሻ መሀመድ÷  እንደ ሀገር ስለ ከተሞች ሴፍቲኔት አሰራር አሁን ካለንበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ትኩረት በማድረግ መሠራት አለበት ብለዋል ።

አያይዘውም በከተሞች እየተተገበሩ ያሉ ማንኛውም ኘሮጀክቶች በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት መቆም የለባቸውም ብለዋል።

ከዚያም ባለፈ ሠራተኞቹ ከበሽታው የሚከላከሉበት ግብአት ሊሟላላቸው እንደ ሚገባ  ገልጸው÷ ለዚህም የኮንስትራክሽን ፕሮቶኮል ወጥቶ ለክልሎች መውረዱን ሚኒስትሯ  መናገራቸውን ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.