Fana: At a Speed of Life!

ዛሬ ምሽት የ5 ሺህ ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር ይደረጋል

 

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ከምሽቱ 3 ሰዓት ከ50 የ5 ሺህ ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር ይደረጋል።

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣እጅጋየሁ ታዬ፣ አትሌት መዲና ኢሳና አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በውድድሩ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ አትሌቶች ናቸው።

አትሌት ጉዳፍ በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር የወርቅ እንዲሁም አትሌት እጅጋየሁ የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘታቸው ይታወቃል።

ዛሬ ጠዋት በተደረገ የሴቶች ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።

በውድድሩ አትሌት አማኔ በሪሶ 1ኛ በመሆን ስታጠናቅቅ አትሌት ጎይተቶም ገብረስላሴ 2ኛ በመሆን የብር ሜዳልያ አስገኝታለች።

በሃንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ ባለው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ እስከ አሁን 2 የወርቅ፣ 4 የብር እና 2 የነሐስ በአጠቃላይ ስድስት ሜዳሊያዎችን በማግኘት አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ሻምፒዮናው ነገ ይጠናቀቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.