Fana: At a Speed of Life!

ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረ ማርያም ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጊዜያዊ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረ ማርያም ከግብጽ ጋር ለሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ለ23 ተጨዋቾች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዚህ መሰረትም ፡-

በግብ ጠባቂነት፡-  ሰኢድ  ሃብታሙ፣ አቡበከር ኑራ እና ቢኒያም ገነቱ

በተከላካይ ስፍራ፡-   ሄኖክ አዱኛ፣ አለምብርሃን ይግዛው፣ ሚሊዮን ሰለሞን፣ አስቻለው ታመነ፣  ምኞት ደበበ፣ አማኑኤል ተርፋ፣ ረመዳን የሱፍ እና ፍራኦል መንግስቱ፣

በመሃል ክፍል፡-  ጋቶች ፓኖም፣ አማኑኡል ዮሃንስ፣ ሽምልስ በቀለ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ ቢኒያም በላይ  እና ወገኔ ገዛኸኝ፣

በአጥቂ መስመር፡-   አቤል ያለው፣  ዳዋ ሁጤሳ ፣ ቸርነት ጉግሳ፣  ፍጹም ጥላሁን  እና ሃብታሙ ታደሰ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ማክሰኞ ነሐሴ 23 ቀን ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል ተገኝተው ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ሪፖርት እንዲያደርጉ ፌዴሬሽን አሳስቧል፡፡

ጨዋታው የፊታችን ጳጉሜን 3 በግብጽ የሚደረግ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.